BBC News, አማርኛ - ዜና
ቀጥታ, ትራምፕ በኢራኗ ወሳኝ ደሴት ላይ የሚገኝ "እያንዳንዱ ወታደራዊ ዒላማ" መውደሙን ተናገሩ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ገጻቸው ላይ "የአሜሪካ ሠራዊት በመካከለኛው ምሥራቅ ታሪክ ውስጥ ከተፈጸሙት እጅግ ከባድ የቦምብ ድብደባዎች አንዱን ፈጽሟል" ሲሉ ከባድ ጉዳት መድረሱን ተናገሩ።
ዜና
"ሰርገኛ መጣ. . ." ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን የማዘጋጀት አቅሙ አላት?
የአፍሪካ ዋንጫ በሚቀጥለው የአውሮፓውያኑ ዓመት በኬንያ፣ በታንዛኒያ እና በኡጋንዳ በጥምረት ይዘጋጃል። የአፍሪካ ዋንጫ በ2028 ድጋሚ ይካሄዳል። ይህ በየሁለቱ ዓመቱ የሚዘጋጀው የአህጉሪቱ የእግር ኳስ ውድድር የመጨረሻው መርሃ ግብር ይሆናል። ካፍ ከ2028 በኋላ ውድድሩን በየአራት ዓመቱ ለማድረግ ወስኗል። ኢትዮጵያ ለብቻዋ ደቡብ አፍሪካ እና ቦትስዋና ደግሞ በጥምር የ2028ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት ያላቸውን ፍላጎት ይፋ አድርገዋል። ለመሆኑ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የማዘጋጀት አቅም አላት? ካፍ የሚጠይቀው መስፈትስት ምንድነው?
የአማራ ክልሉ ፋኖ በአሜሪካ መንግሥት የተገለጸበት "ደረጃ ሦስት የሽብር ቡድን" ምንድነው?
የአሜሪካ ኢሚግሬሽን እና ጉምሩክ ሕግ አስፈጻሚ መሥሪያ ቤት "ራሱን የፋኖ አባል አድርጎ" የገለጸን ሰለሞን ቦጋለ የተባለ ግለሰብ ወደ ኢትዮጵያ ማባረሩን አስታውቋል። የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ላይ እየወሰደ ያለውን ጠንካራ እርምጃዎች የሚያስፈጽመው ይህ መሥሪያ ቤት፤ ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ ግለሰቡ ላይ ከባድ ውንጀላዎችን አቅርቧል።
በአሜሪካ በሽብር ድርጅትነት የተፈረጀው የሱዳን ሙስሊም ብራዘርሁድ ማን ነው?
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በጄነራል አል ቡርሐን ከሚመራው የሱዳን ጦር ሠራዊት ጋር ግንኙነት ያለውን የሱዳኑን ሙስሊም ብራዘርሁድ ቡድን በተለየ ሁኔታ ዓለም አቀፍ ሽብርተኛ በማለት ከመጋቢት 7/2018 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ የውጭ የሽብር ቡድን በሚል እንደፈረጀው አስታውቋል። ለመሆኑ ይህ ቡድን ማን ነው? በሱዳን ውስጥስ ያለው ሚና ምን ያህል ነው?
ኢራን በመካከለኛው ምሥራቅ ፍርሃት የፈጠረችበት ርካሹ ድሮን
አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት መክፈታቸውን ተከትሎ በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ጦርነት እየተካሄደ ነው። ኢራን እየተፈጸመባት ላለው ጥቃት አጸፋውን በቀጣናው ባሉ የአሜሪካ ወዳጅ አገራት ላይ እየፈጸመች ነው። ለዚህ ደግሞ ኢራን ርካሽ እና ውጤታማ የሆኑትን ሻሂድ-136 የተባሉ አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖችን በስፋት እየተጠቀመች ነው። ይህ በምሥል እና በቪዲዮ የተደገፈው ዘገባ ስለድሮኖቹ ምንነት ይተነትናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጦርነት ውጥረት ውስጥ ወዳለችው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ገቡ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢራን ጦርነት አለመረጋጋት ውስጥ ወደ ገባው መካከለኛው ምሥራቅ ተጉዘው የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ገቡ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 3/2018 ዓ.ም. ወደ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የተጓዙት ለሥራ ጉብኝት እንደሆነ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ገልጿል።
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናልን ይቀላቀሉ
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቪድዮዎች
ቪዲዮ, አሜሪካ እና ሩሲያ አመሳስለው ስለሠሩት የኢራኑ ሻሂድ ድሮን ምን ይታወቃል?
ሻሂድ-136 የተባሉት ድሮኖች ከዒላማቸው ጋር በሚጋጩበት ጊዜ የሚፈነዱ ፈንጂዎችን ይዘው ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳሉ። እስካሁን በአሜሪካ ወታደሮች ላይ እጅግ የከፋው ጉዳት የደረሰው አንድ ድሮን በኩዌት የሚገኝ ጦር ሰፈርን መትቶ ስድስት የአሜሪካ ወታደሮች በመገደላቸው ነው። ለመሆኑ ይህ ድሮን እንዴት በመካከለኛው ምሥራቅ ፍርሃት ሊፈጥር ቻለ?
ቪዲዮ, የአራኑ ኃያል ሰው አያቶላህ ኻሜኒ ማን ናቸው? ሥልጣናቸውስ ምን ያክል ጠንካራ ነው?
ኃያሉ የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ እስራኤል እና አሜሪካ በቅንጅት በፈጸሙት ጥቃት መገደላቸው ተረጋግጧል። ከ35 ዓመታት በላይ ኢራንን የመሩት ኻሜኒ በእስላማዊ ሪፐብሊኳ ኢራን መንግሥት ውስጥ የነበራቸው ሚና እጅግ የጎላ ነበር። ጠቅላይ መሪው ከየት ተነስተው ምዕራባውያን በተለይ የአሜሪካ እና የእስራኤል ዒላማ አስከመሆን ደረሱ?
ቪዲዮ, ቱርክን ወደ ኦቶማን ዘመን ዝናዋ ለመመለስ የሚጥሩት ኤርዶዋን ምን እያደረጉ ነው?
ቱርክ ከኦቶማን ግዛተ መንግሥት መውደቅ በኋላ እንደ አገረ መንግሥት ከተመሠረተች 100 ዓመታት አለፋት። የቱርክ አባት በመባል የሚታወቁት አታቱርክ፣ አገራቸውን ከሃይማኖት ገለልተኛ እና ዘመናዊ እሳቤን እንድትላበስ መሠረት ጥለዋል። በዘመናዊው ዓለም መድረክ ጉልህ ተጽዕኖ ያላቸው የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን እንደ ኦቶማን ዘመን ሁሉ ቱርክን በዓለም ኃያል ለማድረግ እየጣሩ ነው። ይሳካላቸው ይሆን?
ቪዲዮ, ኢትዮጵያ የባሕር በር “በባሌም ሆነ በቦሌ ማግኘቷ አይቀርም”- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር መንግሥታቸው ከኤርትራ ጋር ስለገባበት ቅራኔ አጀማመር ከዚህ በፊት ያልተናገሩትን ጉዳይ እማኞችን ጠቅሰው ተናግረዋል። በተጨማሪም በሁለቱ አገራት መካከል ለተፈጠረው መቃቃር ሌላ ምክንያት የሆነው የኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ፍላጎት “በባሌም ሆነ በቦሌ” የሚሳካ ነው በማለት በአርግጠኝነት ነው ተናግረዋል።
ቪዲዮ, ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስለሕዳሴ ግድብ እስካሁን ምን አሉ?
ከቀናት በፊት በአባይ (ናይል) ጉዳይ ኢትዮጵያ እና ግብፅን ለማደራደር ጥያቄ ያቀረቡት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ኢትዮጵያ የናይል ወንዝ "ፍሰትን የሚያስቆም ግድብ" ሠርታለች አሉ። በዚህም ምክንያት ግብፅ ከናይል ወንዝ "በቂ ውሃ እንደማታገኝ" የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ፤ ይህንን ጉዳይ "መፍታት ይኖርብኛል" ሲሉ ተደምጠዋል። ለመሆኑ ፕሬዝዳንቱ በተለያዩ ወቅቶች በጉዳዩ ዙሪያ ምን ተናገሩ?
ቪዲዮ, የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ምን ማለት ይሆን?
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ አቅራቢያ 'አቡሴራ' በተባለ አካባቢ የሚገነባው አዲስ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ቅዳሜ ጥር 2/2018 ዓ.ም. መሠረተ ድንጋይ ተቀምጧል። 12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚወጣበት የአውሮፕላን ማረፊያ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ሲጠናቀቅ፣ በዓመት 60 ሚሊዮን መንገደኞችን ማስተናገድ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። 3,500 ሔክታር መሬት የሚሸፍነው ይህ ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ አውሮፕላን ማረፊያ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ በዓመት 110 ሚሊዮን መንገደኞችን ያስተናግዳል ተብሏል።
ቪዲዮ, ከፍተኛ የነዳጅ ሀብት ያላት አሜሪካ ለምንድን ነው በሌሎች አገራት ነዳጅ ላይ ዐይኗን የጣለችው?
አሜሪካ ከፍተኛ የነዳጅ ክምችት ቢኖረትም በሌሎች አገራት ውስጥ ባሉ የነዳጅ ክምችቶች ላይ ዘወትር ትረኩት ደታርጋለች። ለዚህ በበርካታ አገሮች ጦርነት ውስጥ በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ ስትሳተፍ ቆይታለች። በቅርቡም በቬንዙዌላ ሰጥ ቀጥተኛ ወታደራዊ እርምጃ በመውሰድ መሪዋን ይዛ ወስዳለች። ከዚያም በኋላ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቬንዙዌላ የነዳጅ ሀብት ላይ አሜሪካ ያላትን ፍላጎት በይፋ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ተደምጠዋል።
ቪዲዮ, “ጦርነትን በተግባር እናውቀዋለን” ፕሬዝዳንት ኢሳያስ
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከአገራቸው ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ላለው ውጥረት እና ለተፈጠረው ችግር ከጀርባ ሆኖ የሚገፋ ወገን እንዳለ ተናግረዋል። ጦርነት ሊከሰት የሚችልበት እድል እንዳለ የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ ለዚህም ዝግጁ መሆናቸውን በመግለጽ “ጦርነትን በተግባር እናውቀዋለን” ብለዋል።
አነጋጋሪ ጉዳይ
ኢትዮጵያ ይበልጥ የምትጠቀመው ከማን ብትወዳጅ ነው? ከቱርክ ወይስ ከእስራኤል?
ቱርክ እና እስራኤል በዓለም አቀፉ የፖለቲካ መድረክ በተቃርኖ የሚንቀሳቀሱ አገራት ናቸው። ኢትዮጵያ ደግሞ ከሁለቱም አገራት ጋር የረዥም ጊዜ ወዳጅነት አላት። ለመሆኑ ኢትዮጵያ ሁለት ተቃራኒ አቋም ያላቸውን አገራት ፍላጎት እንዴት ማጣጣም ትችላለች? ኢትዮጵያ ካሏት ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ፍላጎቶች አንጻርስ ከየትኛው አገር ጋር ብትወዳጅ የበለጠ ታተርፋለች?
አምነስቲ፤ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት ሴቶችን "በወሲብ ባርነት" ይዘዋል እና "በቡድን ደፍረዋል" ሲል ከሰሰ
ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተቋም አምነስቲ ኢንተርናሽናል፤ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት በሴቶች እና ሴት ልጆች ላይ "የወሲብ ባርነት" እንዲሁም "በቡድን መድፈርን" ጨምሮ የተለያዩ ወሲባዊ ጥቃቶችን ፈጽመዋል ሲል አዲስ ባወጣው ሪፖርት ከሰሰ። ቡድኑ ግን በአባላቱ ላይ የቀረበውን ክስ "መሠረተ ቢስ" ሲል ውድቅ አድርጎታል።
የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ጦርነቱን ማቆም የማይፈልጉት ለምንድን ነው?
የሱዳን አስፈሪ ጦርነት ሦስተኛ ዓመቱን ሊደፍን በተቃረበበት በአሁኑ ጊዜ የጦርነቱ ምክንያት የሆኑ መሠረታዊ ችግሮች መፍትሄ አላገኙም። ዓለም አቀፍ ቁጣ እና ተቃውሞ ተፋላሚዎቹን ለማስገደድ በቂ ካልሆነ፣ ሁለቱ ወገኖች ጦርነቱን እንዲያቆሙ የሚያደርጋቸው ምንድን ነው?
በትግራይ ጦርነት የተሳተፉ ሴቶች የተፈጠረባቸው የአዲስ ጦርነት ስጋት
በትግራይ ክልል ዳግም ጦርነት ይቀሰቀሳል ብለው በርካቶች ይሰጋሉ። አበባ ከዚህ ቀደም በነበረው ጦርነት በትግራይ ሠራዊት ውስጥ ሆና ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ተዋግታለች። ጦርነቱ ከተቋጨ ሦስት ዓመት ቢያልፍም አሁንም ድረስ ጠባሳዋ አልሻረም። "ሁሉንም ነገር አጣሁ" ትላለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ የህወሓት አመራር "ሰፊ ወታደራዊ ዝግጅት" እያደረገ ነው አሉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ የህወሓት አመራር "ሰፊ ወታደራዊ ዝግጅት"፣ "የጦር መሣሪያ ግዥ" እና "ወታደራዊ ቅስቀሳዎችን እያደረገ ነው" ሲሉ በትግርኛ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ከሰሱ። በፌደራል መንግሥት በኩል "በጭራሽ ትግራይ ላይ የሚጀመር ጦርነት እንደሌለ" አረጋግጣለሁ ሲሉም ተናግረዋል።
በአርሲ ዞን ባለፈው ሳምንት ውስጥ ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ምንጮች ተናገሩ
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ባለፈው ሳምንት ውስጥ ታጣቂዎች በፈጸሟቸው ጥቃቶች ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች እና የቤተ ክርስቲያን ኃላፊዎች ለቢቢሲ ተናገሩ። እሁድ ምሽት በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ ሁለት ሰዎች እንደተገደሉ ሦስት የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል።
ኤምሬቶች፣ ቱርክ እና ሳዑዲ ከኢትዮጵያ የሚፈልጉት ምንድን ነው?
የኢትዮጵያ ስም ከተገዳዳሪዎቹ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና ከሳዑዲ አረቢያ ጋር ተያይዞ መነሳት ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል። ለመሆኑ የባሕረ ሰላጤው አገራት ከንግድ እና ኢንቨስትመንት ጀርባ ያሉ ፖለቲካዊ ፍላጎቶቻቸው ምንድን ናቸው? የኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ ወዳጅ የሆነችው ቱርክ ያላት ሚናስ ምንድን ነው?
ባላንጣዎቹ ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የፍልሚያ ሜዳ ያደረጉት የአፍሪካ ቀንድ
በባላንጣነት የሚታየዩት የመካከለኛው ምሥራቅ ኃያላን ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና ወታደራዊ ለውጦች እንዲታዩ ምክንያት እየሆኑ ነው። በተለይ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና ሱዳን የእነዚህ አገራት ዋነኛ የመፎካከሪያ መድረኮች ሆነዋል። በተጨማሪም ቱርክ በቀጣናው ያላት ሚና እየጎላ ነው። ይህ ፉክክር ለአፍሪካ ቀንድ ምን ይዞ ይመጣል?
የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?
የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!
ከየፈርጁ
ብርሃኔ አስፋው፡ ለሴቶች ደኅንነት ባደረጉት ጥረት ለኖቤል ሽልማት እስከመታጨት የደረሱት ኢትዮጵያዊት
ብርሃኔ የመንግሥታቱ ድርጅት የሕፃናት ስምምነት ላይ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን የሚከለክሉ አንቀፆችን አርቅቀዋል፤ በስምምነቱ እንዲካተቱቱም ውትወታ አድርዋል። የሰብዓዊ መብት አርበኛ የሆኑት ወ/ሮ ብርሃኔ 60 ዓመታት የዘለቀ ስኬታማ ትዳርም አላቸው። ወ/ሮ ብርሃኔ አስፋው ለሴቶች ጤና እና ደኅንነት ላበረከቱት አስተዋፅኦ በሽልማት ተንበሽብሸዋል። ድርጅታቸውን አቋቁመው ከተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስቆም ሲታትሩ ያዩ ደግሞ ለኖቤል አጭተዋቸዋል። ቢቢሲ ወ/ሮ ብርሃኔን ስለ ሥራ እና ሕይወታቸው አነጋግሯቸዋል።
ፆም በሰውነታችን ውስጥ የሚያስከትለው ለውጥ እና የሚሰጠው ጥቅም ምንድን ነው?
ለእስልምና እና ለክርስትና እመነት ተከታዮች ዋነኞቹ የፆም ወቅት የሆኑት ረመዳን እና ዓቢይ ፆሞች ተጀምረዋል። የሁለቱም እምነቶነቶች ምዕመናን የፆሙን ጊዜ በየራሳቸው ሥርዓት እና ደንብ መሠረት የሚከውኑት ሲሆን፣ በየዕለቱ ለረጅም ሰዓታት ከምግብ እና ከውሃ ርቀው ይቆያሉ። በዚህ ጊዜ ታዲያ ፆም በሰውነት ላይ ምን ለውጥን ያስከትላል? ምንስ ጥቅም አለው?
ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል ስጋት ውስጥ መኖር
ግጭቶች በሰው ሕይወት እና አካል እንዲሁም በንብረት እና በመሠረተ ልማቶች ላይ ከሚያደርሱት ጉዳት ባሻገር በሰዎች አካላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ጤና እና ደኅንነት ላይ ከባድ ተጽእኖን እንደሚያስከትል ባለሙያዎች ይናገራሉ። እንዲህ ባለው ሁኔታ ውስጥ ስንሆን የሚከሰቱ ሥነ ልቦናዊ ለውጦች ምንድን ናቸው? ለመቋቋምስ ምን ማድረግ እንችላለን?
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
አጃኢብ!
የኒውክሌር ጦርነት ሊያስነሳ የነበረው የኖርዌይ የአየር ሁኔታ ምርምር ሮኬት
በአውሮፓውያኑ ጥር 25/1995 ኖርዌይ 'ኖርዘርን ላይትስ' የተባለውን የሰማይ ላይ ደማቅ ብርሃን ለማጥናት የተኮሰችውን ሮኬት ሩሲያ በስህተት ወደ ሞስኮ የተወነጨፈ የኒውክሌር ሚሳዔል እንደሆነ ቆጥራው ነበር። ከቀዝቃዛ ጦርነት ስሜት ገና በቅጡ ያላገገመው ዓለም በአንድ የአዘቦት ቀን ለሰዓታት የቆየ በድጋሚ ጦርነት ውስጥ የመግባት አስከፊ ስጋት ተጋርጦባት ነበር።
ሺህ ዘመናት የተሻገረው ኩል ለጤና እና ለውበት ያለው ጥቅም
የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ተቋም በዓለም የማይዳሰሱ ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ ኩልን አካቶታል።
የእስራኤል እና የኢራን ግጭት
አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት፡ ዋና ዋና እውነታዎች በካርታ
አሜሪካ እና እስራኤል በፈጸሙት ጥቃት የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ሲገደሉ፤ ኢራን በመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ላይ ጥቃት መፈጸም ቀጥላለች። እየተካሄደ ስላላው ጦርነት፣ ስለ ኢራን እና ባለፉት ቀናት ስለተከሰቱ ዋና ዋና ነገሮች ሊያውቋቸው የሚገቡ እውነታዎች በምሥል እዚህ ይመልከቱ።
የኢራን ወዳጅ፣ የእስራኤል ጠላት የሆነው ሄዝቦላህ ማን ነው? እንዴትስ ተመሠረተ?
ሄዝቦላህ መልከ ብዙ ነው። የፖለቲካ ፓርቲ ብቻ አይደለም። ማኅበራዊ አገልግሎት ላይ ይሠራል፣ ፖለቲካ ላይ ይሳተፋል፤ ሚሊሻም ነው። ድንበር ተሻጋሪ ወታደራዊ ክንፍም አለው። ይህ መልከ ብዙነቱ በሊባኖስም ከሊባኖስ ውጪም አቅም ፈጥሮለታል። ለመሆኑ ሄዝቦላህ ማን ነው? እንዴትስ ለእስራኤል ፈተና ሊሆን ቻለ?
ኢራን እና እስራኤል መቋጫ ያላገኘ ደመኛ ጠላቶች የሆኑት ለምንድን ነው?
ኢራን ከግብፅ ቀጥላ ለእስራኤል እውቅና በመስጠት ሁለተኛዋ እስላማዊ አገር ነበረች። ነገር ግን ከኢራን እስላማዊ አብዮት በኋላ ይህ ግንኙነት ተበላሽቶ ከአራት አስርታት በላይ በጠላትነት እየተያዩ ቆይተዋል። ለመሆኑ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ወደ ደመኛ ጠላትነት ለምን ተሸጋገረ?
የተመለሱ ጥያቄዎች
"ተወዳጇ እና ደስተኛዋ ልጄ እንዴት በራሷ ላይ ወሰነች?" - በቲክ ቶክ እና በእኩዮቿ ጫና ራሷን ያጠፋቸው ኢትዮጵያዊት ታዳጊ
አቶ ነብዩ ማኅበራዊ ሚዲያ በታዳጊ ልጆች ላይ የሚያስከትለውን ተጽእኖ በተመለከተ መራራ የሆነ ልምድ ነው ያላቸው። የ13 ዓመቷ ልጃቸው ፊዮሬላ ላይ ምንም ዓይነት ምልክት ሳይመለከቱ በእኩዮቿ ጫና እና በማኅበራዊ ሚዲያ ግፊት ባላሰቡት ጊዜ ልጃቸው እራሷን አጥፍታ አግኝተዋታል።
አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ ቢሾፍቱ እንዲሆን ለምን ተመረጠ?
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ግዙፍ የሚባለው የአውሮፕላን ማረፊያ ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር ያህል በሚርቅ ቦታ ላይ ለመገንባት ሥራ ጀምራለች። ይህ አውሮፕላን ማረፊያ መሃል አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኘው በብዙ እጥፍ የሚበልጡ መንገደኞችን ያስተናግዳል ተብሏል። ይህንን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ለምን አሁን መገንባት አስፈለገ? ቦታውስ ለምን ተመረጠ?
ሌላ ዕይታ
ቢቢሲ አማርኛን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ይከታተሉ
ከማኅደራችን
ማርበርግ ቫይረስ: የመጀመሪያው ታማሚ እና ሦስት መሪዎቿን ያጣችው የጂንካ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን
ከሌሊት ወፎች የሚነሳው የማርበርግ ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተገኘ አንድ ወር ሊደፍን ጥቂት ቀናት ቀርተውታል። የጤና ሚኒስቴር፤ እንዴት በሽታው በጂንካ ከተማ ሊነሳ እንደቻለ እስካሁን አልገለጸም። ለመሆኑ በጂንካ የመጀመሪያው ታማሚ ማን ነበር? የበሽታው መነሻ የሆኑት የሌሊት ወፎችን እና የመጀመሪያውን ታማሚስ ምን አገናኛቸው? ቢቢሲ ባደረጋቸው በርካታ ቃለ መጠይቆች ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ የሚሆኑ መረጃዎች አሰባስቧል።
"ቢገድሉኝ ይሻል ነበር"፡ የሴቶችን ሕይወት እያበላሸ ያለው የተዘነጋው የአማራ ክልል ጦርነት
ከሁለት ዓመት በላይ የሆነው በአማራ ክልል በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በሚካሄደው ግጭት ሰላማዊ ሰዎች ከባድ ዋጋ እየከፈሉ ነው። ግጭቱ በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት ባሻገር በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እና ሰቆቃ ትኩረትን አላገኘም። ቢቢሲ ለወራት ባካሄደው ክትትል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሴቶች የመደፈር እና የወሲባዊ ጥቃት ሰለባ መሆናቸውን መረጃ አግኝቷል።
በብርሌ ፍቅር የወደቁት ፈረንጅ 'ብርሌ ውስጥ የኢትዮጵያ ታሪክ አለ' ይላሉ
ሰሞኑን አረቄ ብሔራዊ አጀንዳ ሆና የማኅበራዊ ሚዲያ አናት ላይ ወጥታ ነበር። ጠጅ ቢሆን አናት ላይ አይወጣም፤ ወደ ጉልበት ነው የሚወርደው። ጠጅ ለመጨረሻ ጊዜ ጉዳይ ሆኖ የሥነ መንግሥቱ አናት ላይ ወጥቶ፣ 'ብሔራዊ አጀንዳ' የነበረው በዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ዘመን ነው። ድሮ ጠጅ በብርሌ ይቀርብ ነበር። ከዚያ በብርሌ ይጠጣ ጀመር። ጠጅ ግን እንደ አረቄ ማንም ‘ተራ ዜጋ’ ብድግ አድርጎ አያንደቀድቀውም።ብርሌ ውስጥ የመደብ ታሪክ አለ። የዘመን ታሪክ አለ። የጭሰኛና የመሳፍንት ታሪክ አለ። ያልተሳከረ።
ዓለምን የሚዞረው ኢትዮጵያዊ ከዩቲዩብ ምን ያህል ያገኛል?
ከተከፈተ በዚህ ወር 20 ዓመት የሆነው የቪዲዮ ማጋሪያው የማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ ዩቲዩብ ለብዙዎች የተለያዩ አጋጣሚዎችን ፈጥሯል። ከእነዚህም መካከል አቤል ብርሃኑ አንዱ ነው፤ በዩቲዩብ አማካኝነት 62 ሀገራትን ዟሯል። ያልረገጠው አህጉር አንታርቲካን ብቻ ነው። ሁሉንም የአሜሪካ ግዛቶች አካሏል። ከዘጠኝ ዓመታት በላይ ዩቲዩብ ላይ የቆየው አቤል ከዩቲዩብ ምንያህል ያገኛል?
ቪዲዮ, በአርሰናል ‘ፍቅር የወደቁት’ የ65 ዓመቷ እናት፡ ወይዘሮ እቴቱ ማሞ, ርዝመት 3,29
ከእንግሊዝ ታላላቅ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው የአርሰናል የልብ ደጋፊ የሆኑት ወ/ሮ እቴቱ ማሞ የ65 ዓመት እናት ናቸው። ላለፉት 20 ዓመታት አርሰናልን ያለማቋረጥ ደግፈዋል። እንደብዙዎቹ የቡድኑ ደጋፊዎች ዘንድሮ አርሰናል ዋንጫ ባለማንሳቱ ቢከፉም ድጋፋቸው ግን እንደሚቀጥል ይናገራሉ። ከሁሉም ተጫዋቾች ይልቅ እሳቸው ገብረኢየሱ ለሚሉት ለጋብሬል ጀሱስ እና ለቡካዮ ሳካ የተለየ ፍቅር አላቸው።
እነ ሞገስ አስገዶም፣ አብረሃ ደቦጭ፣ ፕ/ር አስራት ወልደየስ፣ ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም፣ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር የተማሩበት ተፈሪ መኰንን
ተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት ታሪክ የዘመናዊት ኢትዮጵያ ንድፍ እንደማለት ነው። ላለፉት 100 ዓመታት ታላላቅ ሰዎችን ወልዷል። ለመኾኑ ይህ ተማሪ ቤት እነማንን አፈራ? ይህ ሐተታ በ100 ዓመት ታሪኩ ውስጥ በአንድም ሆነ በሌላ አሻራቸውን ያሳረፉትን ግለሰቦች ያወሳል፤ ከካናዳዊያን ጄስዊቶች እስከ ከንቲባ አዳነች አበቤ፤ ከቱጃሩ ራስ ኃይሉ ተክለሃይማኖት እስከ ቢሊየነሩ ሼክ አላሙዲን፣ ከሐኪም ወርቅነህ እሸቴ እስከ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ።
ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት የምትገኘው አሊ ዶሮ እና አካባቢዋ ለምን የእገታ ማዕከል ሆኑ?
ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በሕዝብ እና በጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እና እገታዎች ተበራክተዋል። ይህ ክስተት ደግሞ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው የሰሜን ሸዋ አካባቢ በተደጋጋሚ ሲከሰት ቆይቷል። በተለይ አሊ ዶሮ የሚባለው ቦታ የጥቃት እና የእገታ ማዕከል ሆኗል እየተባለ ነው። ቢቢሲ በተለይ ይህ ቦታ ለምን የመንገደኞች እና የአሽከርካሪዎች ‘የሞት ቀጣና’ ሆነ? በሚል ለወራት የዘለቀ ምርመራ አድርጓል።
ባይተዋር ከተማ፡ “ፒያሳ፣ ካዛንቺስ... ሰፈሬ አልመስል አሉኝ”
ባለፉት ዓመታት በአዲስ አበባ በቅርስነት ተመዝግበው የነበሩ እንዲሁም ሌሎችም ታሪካዊ ሕንጻዎች፣ ቤቶች እና አካባቢዎች እንደ ዋዛ አፈር ለብሰዋል። በዚህ ዘገባ፣ አንድን ሕንጻ ወይም ቤት ቅርስ አልያም ታሪካዊ ሥፍራ ለማለት መስፈርቱ ምንድን ነው? የታሪካዊ ሕንጻዎች እና ቤቶች መፍረስ በታሪክ፣ በነዋሪዎች ሥነ ልቦና፣ በኪነ ሕንጻ እና በማኅበራዊ መስተጋብር ላይ ምን ጫና ያሳድራል? ቅርሶች እና ታሪካዊ ሥፍራዎችን እንዴት ጠብቆ ማደስ፣ ማዘመን፣ መልሰው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ማድረግ እንዲሁም ከሌሎች ግንባታዎች ጋር ጎን ለጎን እንዲሄዱ ማድረግ ይቻላል? የሚሉት እና ተያያዥ ነጥቦች ተዳስሰዋል።
“ሰው መሃል ሆኜ ሁሉም ጨካኝ ሆኖብኝ ነበር” - የፀጋ በላቸው ዘጠኝ የጠለፋ ቀናት
ግንቦት 2015 ዓ.ም. የተፈጸመው የፀጋ በላቸው ጠለፋ ብዙዎችን ያስቆጣ፣ መነጋገሪያም የሆነ የወንጀል ድርጊት ነበር። ፀጋ፤ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት ተጠልፋ ያሳለፈቻቸውን ቀናት በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቢቢሲ በዝርዝር ተናግራለች። ከቢቢሲ ጋር በነበራት ዘለግ ያለ ቆይታ፤ ስለተጠለፈችበት መንገድ እና ስላሳለፈቻቸው ዘጠኝ ቀናት በዝርዝር ተርካለች። ከጠለፋው ነጻ የወጣችበት መንገድም አስቀድሞ በክልሉ መንግሥት ከተገለጸው የተለየ እንደሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናግራለች። ለምን ከኢትዮጵያ እንደተሰደደች እና ስለ ቀጣይ ዕቅዶቿም እንዲሁ አጋርታለች።
". . . ከምድሩ ይልቅ የሰማዩን መንገድ ለመምረጥ ተገደናል" እገታ ያሰጋቸው መንገደኞች
ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ የሚካሄዱ ግጭቶች እና በታጣቂዎች የሚፈጸሙ እገታዎች ዜጎች በፈለጉት ጊዜ እና መንገድ በአገሪቱ ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ ብርቱ ስጋት ፈጥሮባቸዋል። በተለይ ደግሞ የመንገደኞች ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን በማድረግ የሚፈጸሙት ያላባሩ እገታዎች በዋነኞቹ የአገሪቱ ክልሎች ውስጥ እንቅስቃሴን አዳጋች አድርገውታል። በዚህም ሳቢያ አቅሙ ያላቸው እና የግድ የሆነባቸው ሰዎች ፊታዎችን ወደ አየር ትራንስፖርት አዙረዋል።
"'ቁርጭምጭሚት' የሚለው ቃል ያስቀኛል'' ለ23 ዓመታት ለፈረንጆች አማርኛን ያስተማረችው ፖላንዳዊት፣ ዶ/ር ኤቫ ቮልክ-ሶሬ
ፓላንዳዊቷ ዶ/ር ኤቫን የአማርኛ ቋንቋን ከ40 ዓመት በፊት ተምራ በዲግሪ ከተመረቀች በኋላ ከሃያ ዓመታት በላይ በማስተማር በርካቶችን በአማርኛ ቋንቋ ዲግሪ አስይዛለች። የምታስተምርበት ዩኒቨርስቲ ወደ 80 ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ አማርኛን እያስተማረ ነው። አማርኛ ቋንቋን “ፏፏቴ ነው” የምትለው ዶ/ር ኤቫን በአገሯ በአማርኛ አስተርጓሚነት ትሠራለች። ለመሆኑ እንዴት ከአማርኛ ጋር ተዋወቀች?
"ብልጽግናዎች ይዘውን እንዲጠፉ አንፈቅድም፤ አገራችን ሕዝባችን ነው፤ ዝም አንላቸውም" - ጃዋር መሐመድ
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ካላቸው ፖለቲከኞች መካከል ጃዋር መሃመድ አንዱ ነው። ለዓመታት ያህል በኦሮሚያ የነበሩ ትግሎችን እንዲሁም ተቃውሞዎችን ከጀርባም ሆነ ከፊት ሆኖ በማስተባበር እና በመምራት ግንባር ቀደም ነው።የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ አመራሩ ጃዋር ከትውልድ አንስቶ በፖለቲካ ህይወቱ የተጓዘበትን ህይወቱ ላይ የሚያጠነጥን 'አልጸጸትም' የተሰኘውን መጽሐፍ ታህሳስ 10/ 2017 ዓ.ም በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ያስመርቃል። ጃዋር መሃመድ በአገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ፣ በቀጣይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ስለሚኖረው ሚና፣ አገሪቱ ስላለችበት ሁኔታ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ቆይታ አድርጓል።














































































































